የኢኖቬሽን አፍሪካ ስብሰባ በአዲስ አበባ ሊካሔድ ነው

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 17/2017 (ኢዜአ)፦ የኢኖቬሽን አፍሪካ 2025 ስብሰባ ከሚያዚያ 20 እስከ 22 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

ስብሰባው በትምህርት፣ በኢንፎርሜሽን እና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) እና ዲጂታል ክህሎት ላይ ያተኮረ መሆኑን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።


 

የአፍሪካ ሀገራት ሚኒስትሮች በስብሰባው ላይ እንደሚሳተፉም ገልጿል።

ሁነቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የትምህርት ሚኒስቴር እና የስራና ክህሎት ሚኒስቴር በጋራ አዘጋጅተውታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም