መሶብ የአንድ መስኮት አገልግሎት በአንድ ጣራ ስር የተለያዩ የመንግስት አገልግሎቶችን መስጠት ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
መሶብ የአንድ መስኮት አገልግሎት በአንድ ጣራ ስር የተለያዩ የመንግስት አገልግሎቶችን መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 18/2017(ኢዜአ)፦ መሶብ የአንድ መስኮት አገልግሎት በአንድ ጣራ ስር የተለያዩ የመንግስት አገልግሎቶችን መስጠት ጀምሯል።
መሶብ የአንድ መስኮት አገልግሎት በአንድ ጣራ ስር የተለያዩ የመንግስት አገልግሎቶችን በማጣመር ምርጥ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የሚሰጥ አገልግሎት ነው።
የአሰራር ስረዓቱ ዜጎች የተሟላ የዲጂታል አማራጮችን በመጠቀም በቀላሉ የተለያዩ የፌደራል ተቋማትን አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
ይህም ባለጉዳዮች ወደ ተለያዩ ቢሮዎች የሚያደርጉትን ምልልስ፣ረጅም የወረፋ ጥበቃ እና ከወረቀት ጋር ተዛማጅ የሆኑ ስራዎችን የሚያሰቀር ነውም ብሏል፡፡
አሁን ሥራ ለጀመረው የሙከራ ፕሮጀክት አስራ ሁለት የፌደራል መንግስት ተቋማት የተቀላቀሉ ሲሆን አርባ አንድ የሚሆኑ የህዝብ አገልግሎቶችንም ማቅረባቸውንም ገልጿል፡፡
አገልግሎቶቹም ከፈቃድ አሰጣጥ ጀምሮ ፋይዳ ድጅታል የመታወቂያ ምዝገባ እና ሌሎችንም ያካተተ መሆኑን ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።
በአጠቃላይ በፓይለት ፕሮግራም በአንድ ስፍራ የ12 ተቋማት 41 አገልግሎቶች በመሰጠት ላይ የሚገኙ ሲሆን ተቋማቱም፦
1. የብሄራዊ መታወቂያ አገልግሎት
2. የኢሚግሬሽን እና የዜግነት አገልግሎት
3. የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት
4. የገቢዎች ሚኒስቴር
5. የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር
6. የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር
7. የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን
8. የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር
9. የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት
10. የኢትዮ ፖስታ
11. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
12. ኢትዮ ቴሌኮም
ሀሉም ተቋማት በቴክኖሎጂ አማካኝነት በትስስር አገልግሎት እየሰጡም ይገኛሉ።