የአማራ ክልል የቴክኖሎጂ፣ የክህሎት እና የተግባራዊ ጥናትና ምርምር የንግድ ትርኢት ሳምንት በኮምቦልቻ ከተማ ተከፈተ

ደሴ፤ ሚያዝያ 19/2017(ኢዜአ)፦ የአማራ ክልል 9ኛው የቴክኖሎጂ፣ የክህሎት፣ የተግባራዊ ጥናትና ምርምር እና የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የንግድ ትርዒት እና የደረጃ ሽግግር ሳምንት በኮምቦልቻ ከተማ ተከፈተ።

የንግድ ትርኢትና የደረጃ ሽግግር ሳምንቱን የከፈቱት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እና የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፋሪሃት ካሚል ናቸው።

በሥነ-ስርአቱ የአማራ ክልል ሥራና ስልጠና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አማረ አለሙ እንደገለፁት ፕሮግራሙ በዘርፉ የተሰማሩ ሙያተኞች የቴክኖሎጂ እውቀታቸውን ማዳበር የሚያስችል ነው።


 

ከዛሬ ጀምሮ ለአምስት ቀናት በሚቆየው የንግድ ትርኢትና የደረጃ ሽግግር ሳምንት 110 በክህሎት፣ 75 የቴክኖሎጂ ተወዳዳሪዎች የሚሳተፉ ሲሆን 57 የፈጠራ ሥራዎችም ለእይታ ይቀርባሉ ብለዋል።

ባለፉት ዓመታት በየተሰማሩበት የሥራ ዘርፎች ለውጥ ያመጡ 345 አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችም ወደ ታዳጊና መካከለኛ ባለሀብትነት ይሸጋገራሉ ብለዋል።

በፕሮግራሙ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን(ዶ/ር)፣ አፈ-ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣በምክትል ርእሰ መሥተዳደር ማዕረግ የከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪ እና የከተሞች እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አህመዲን መሀመድ (ዶ/ር) እና ሌሎች የክልሉ አመራሮች ተገኝተዋል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም